፦ አቶ ሚደቅሳ ከበደ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የተከበሩትን ሃይማኖታዊና የአደባባይ በዓላት ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ላደረው አስተዋጽዖ የሰላም ሰራዊቱን የማነቃቃትና የምስጋና ፕሮግራም አካሄደ ። በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ እንደተናገሩት የሰላም ሰራዊቱ በከተማው ሰላምን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በመስራት የአደባባይ በዓላት በሰላም ተከበረው እንዲጠናቀቁ ሚናው የጎላ በመሆኑ የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ የጸረ ሰላም ሃይሎች አጀንዳዎችን በመቀልበስ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ በመስራት ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቅ መቻሉን ገልጸዋል። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ዋቅጋሪ በበኩላቸው የሰላም ሰራዊት አባላት ከሌሎች መደበኛ የፀጥታ አደረጃጀቶች ጋር በመቀናጀት ሀገራዊ ተልዕኮዎችን በውጤት ያረጋገጡበት አግባብ የላቀ ሚና እንደነበረው በመጠቆም አደረጃጀቱ ህዝባዊ እንደመሆኑም የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ከምንጫቸው በዘላቂነት ለማክሰም በሚደረገው ርብርብ የፀጥታ አደረጃጀቱ የአንበሳውን ድርሻ ተወጥቷል ብለዋል። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ወረዳ 10 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሲሳይ ምንዳዬ በበኩላቸው የሰላም ሠራዊት እና የፀጥታ አካላት ከአመራሩ በመቀናጀት አካባቢያቸውን የመጠበቅ እና ሰላምና ፀጥታን የማረጋገጥ ተግባር በአንድ ማዕከል ስምሪት በመውሰድ በሁሉም ክላስተር እና ብሎክ የሰላምና ፀጥታ የማስከበር ስራ በማጠናከር የአደባባይ በዓላት በህዝቦች አብሮነትና አንድነት እንዲከበሩ ለማድረግ ላስመዘገቡት ውጤት ምስጋና አቅርበው የሰላም ሰራዊቱ እንዲነቃቁ መደረጉ ለቀጣይ የበለጠ ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያደርግ በመሆኑን ገልጸዋል። በስነ ስርዓቱ ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የከተማ ፖሊስ አባላት ፣ የሰላም ሰራዊት አባላት ፣ ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈውበታል። በመጨረሻም የሰላም ሰራዊት አደረጃጀትን ሲደግፉ ለነበሩ አካላት ለህዝባዊ አደረጃጀቶች እና ለፀጥታ አስከባሪዎች የምስጋናና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል። #እኔ_የአካባቢዬ_የሰላም_ዘብ_ነኝ!!