አስተዳደሩ በ3 ወራት በንቅናቄ እየተከናወኑ የሚገኙ የሴቶችና የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ፣ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ተግባራት ፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የገቢ አሰባሰብ ፣ የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት የተከናወኑ ተግባራትን ፣ የገቢ አሰባሰብ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር ገምግሟል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው ሁሉን አቀፍ ለውጥ ለማምጣት ስራዎችን በመደበኛና በንቅናቄ እየተመሩ ይገኛል ያሉ ሲሆን በተለይም የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሀብት አሰባሰብ ፣ የገቢ አሰባሰብ ፣ የኑሮ ውድነት ማረጋጋት ተግባራትን ሁሉም አመራር በትኩረት በመምራትና በመገምገም ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል። የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ በበኩላቸው በንቅናቄ እየተመሩ የመጡ የስራ ዕድል ፈጠራና የከተማ ግብርና ስራዎቻችን በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ በመሆኑ ለስራዎቹ ትኩረት በመስጠት ሁሉንም በ100 ፐርሰንት አፈጻጸም በመጨረስ ኢንተርፕራይዝ ማደራጀት ፣ ስልጠና መስጠተ ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።