እንኳን ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዌብሳይት በሰላም መጣችሁ እያልኩ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አሰተዳደር ነዋሪውን የልማትና መልካም አስተዳደር፤ የአገልግሎት አሰጣጥ የተሳለጥ፤ ተደራሽነቱን ለማስፋት እና ለማዘመን በርካታ ስራዎች እየሰራን እንገኛለን፡፡ የመንግስት እና የፓርቲያችን መርህን መሰረት በማድርግ ሰው ተኮር የልማት ተግባራት የዜጎች ፍታሀዊ ተጠቅሚነት ለማረጋገጥ በኑሮ ውድነትና ገበያን በማረጋጋት ፤በሌማት ትሩፋት፣ በስራ እድል ፈጠራ፣ በማዕድ ማጋራት፣ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታና በሌሎች ሰው ተኮር ተግባራት ተጠቃሚነት ላይ እየሰራን እንገኛለን ። አንዲሁም ለማህበረሰቡ ለኑሮ ምቹ እና ውብ የሆነች ክፍለ ከተማ ለመፍጠር የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች በማልማት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ በከተማችን ከተያዙ ፕሮጀክቶች በቁጥርም በስፋትም በቁጥር አንድ ከሚቀመጡ ክ/ከተሞች አንዱ በመሆን ስፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም በርካታ ዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚና የሙያ ባለቤት የሚያደርግ ስራ በመሰራት ላይ ሲሆን በተጨማሪ በክፍለ ከተማችን የአዲስ አበባ መተንፈሻ ሳንባ እደመሆኑዋ መጠን ፅዱና ውብ የማድረግ በተለያየ ጊዜ ማህበረሰቡን በማሳተፍ በንቅናቄ በአካባቢ ፅዳት ማህበረሰባችን እየሰራ ያለውም ጉዳይ ቀላል የማይባልና በአመለካከት እና በተግባር እየመጡ ያሉ ለውጦችም ቀላል የማይባሉ ለውጦች መተዋል እነዚ እና ሌሎች ሁለንተናዊ የሆነ የልማት ስራችን ላይ ያለውን የነቃ ተሳትፎ ለማህበረሰባችን ትልቅ ክብር እዳለኝ መግለፅ እወዳለሁ ፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን የአገልግሎት አሰጣጥ ስራችን ቀልጣፋና ተደረሽ ለማድረግና ስራና ሰራተኛን ለማገናኘት በዋና ዋና ሴክተሮቻችን የሪፎርም ስራ በመስራት የምደባ ስራ የተሰራ ሲሆን የሰው ኃይል በአቅም በክህሎት በቂ ከማድረግና የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ከማዘመን አንፃር የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት በመዘርጋት የተቀናጀ የመረጃ ልውውጥ ስርዓትን እንዲኖር በማድረግ ተገልጋዮችን ከእንግልት በማላቀቅ በቴክኖሎጂ አገልግሎት አማራጭን ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡ እነዚህንና እነዚህን መሰል በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ በትኩረትና በጥራት አዲሁም በመፍጠርና በመፍጠን ስራዎቻችን እየሰራን ሲሆን ሌሎች ክፍለ ከተማችን በሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች የህብረተሰቡን ጥቅም ለማረጋገጥ በምናደርገው ጥረት ሁሉም የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ እያሳሰብኩ በክፍለ ከተማችን ብሎም በከተማችን እድገት በአብሮነትና በጋራ እንድንሰራ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡
ወንዶች
ሴቶች
ጠቅላላ ነዋሪዎች
የጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ
የጉለሌ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የጽ/ቤት ኃላፊ
የጉ/ክ/ከ/አስ/ምክ/ዋ/ስ/አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ
የጉ/ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ምክትል እና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ
Posted on 2025-02-07 01:16:41
የጉለሌ ወረዳ 9 አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን በካሜራ የተደገፈ ምርጥ ተሞክሮ ማስፋቱ ተገለጸ ።
Posted on 2025-02-07 01:15:23
የመማር ማስተማር ስነ ዘዴ ተግባራዊ በማድረግ የነገ ሃገር ተረካቢ ዜጋ መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ።
Posted on 2025-02-07 01:13:22
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በንቅናቄና በመደበኛ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ዙሪያ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር ገምግሟል።
Posted on 2025-02-07 01:12:20
የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ ሰው ተኮር ስራዎችን እየጎበኙ ነው።