የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ለመንግስት ትምህርት ቤቶች ቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን የመማር ማስተማር ስነ ዘዴ ስልጠና ሰጥቷል። በስልጠናው በዋናነት የቀዳማይ ልጅነት ምንነትና አስፈላጊነት ፣ በጨዋታ የማስተማር ስነዘዴ አተገባበርና ምቹ የመማሪያ አካባቢ መፍጠር ፣ እንዲሁም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ምንነትና የትምህርት አመራር ክትትልና ድጋፍ አሰጣጥ ላይ ትኩረት ያደረጉ ርዕሰ ጉዳዮች የሚሰጥ መሆኑ ተመላክቷል:: የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራ እንደተናገሩት በከተማ ደረጃ እንደ ክፍለ ከተማ በትምህርት ዘርፉ ላይ የነበሩ ስብራቶችን ለመጠገን በአዲሱ የትምህርት ፎኖተ ካርታ በመተግበር ብቁ መምህራን ብቁ ዜጋ ለማፍራት እየተሰራ ይገኛል የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምራን ስልጠና በስነ ልቦናቸዉ እንዲበቁ ፣ ንቁ እንዲሁም በአካል የዳበሩ እንዲሆኑ ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል። ኃላፊው አክለውም ስልጠናውን የሚወስዱ መምህራን በጥብቅ ዲሲፕሊን በመመራት ስልጠናውን እንዲከታተሉና በሚፈለገው ልክ በመረዳትና የወሰዱትን እውቀትና ክህሎት ለሌሎች ለማስተላለፍ የሚያስችል አቅም እንዲያዳብሩ ገልጸዋል ::