Loading...

ዝርዝር ዜና

ማህበራዊ ማህበራዊ

በክፍለ ከተማው በ2ኛው ዙር ከሚለሙ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክት የአዲስ ለአዲስ የወንዝ የልማት ፕሮጀክት ተነሺ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል የምትክ ቦታ እና ምትክ የቀበሌ ዕጣ የማውጣት መርሃ ግብር ተከናወነ።


በክፍለ ከተማው በ2ኛው ዙር ከሚለሙ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክት የአዲስ ለአዲስ የወንዝ የልማት ፕሮጀክት ተነሺ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል የምትክ ቦታ እና ምትክ የቀበሌ  ዕጣ የማውጣት መርሃ ግብር ተከናወነ።

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት አስተዳደር ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአዲስ ለአዲስ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ነዋሪዎች መካከል ለ79 የምትክ ቦታ የዕጣ እና 223 ምትክ የቀበሌ ቤት ማውጣት ስነ ስርዓት ተከናወነ። በዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራ ፣ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው በ2ኛ ዙር የአዲስ ለአዲስ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት መልሶ ማልማት ተነሺ የሆኑ ነዋሪዎች ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የምትክ ቦታና የቀበሌ ቤቶች ዕጣ ማውጣት አካሄደናል ያሉ ሲሆን ነዋሪው ለልማቱ እያሳየ ላለው አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ መሬት አስተዳደር ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ካሳሁን ጥላሁን እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው የተነሺዎችን ፍትሃዊ የሆነ አሰራርን በጠበቀ መልኩ በመስራት ላይ እንገኛለን በዚህም ካሳ የተፈለላቸውም ያልተከፈላቸው የአዲስ ለአዲስ የወንዝ ዳርቻ የልማት ፕሮጀክት ተነሺ መካከል ለሆኑ ነዋሪዎች መካከል 79 ለሚሆኑ በዛሬው ዕለት የምትክ ቦታ ዕጣ የማውጣት ስነ ስርዓት አውጥተናል ብለዋል። የጉለሌ ክፍለ ከተማ የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እምሩ ሽፈራው እንደተናገሩት የበክፍለ ከተማው በ2ኛው ዙር እየለማ ለሚገኘው በመልሶ ማልማት በቀበሌ ቤት ፣በኪራይ ቤቶች ድርጅት ፣ የቤተ ክህነት ስር ለነበሩ ቤቶች የኮሪደር ልማት 18 ነዋሪዎችና የአዲስ ለአዲስ የወንዝ ዳርቻ 223 ነዋሪዎች ዕጣ አውጥተዋል ብለዋል።

Search
Recent News