Loading...

ዝርዝር ዜና

ማህበራዊ ማህበራዊ

የጉለሌ ወረዳ 9 አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን በካሜራ የተደገፈ ምርጥ ተሞክሮ ማስፋቱ ተገለጸ ።


የጉለሌ ወረዳ 9 አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን በካሜራ የተደገፈ ምርጥ ተሞክሮ ማስፋቱ ተገለጸ ።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት አገልግሎትን ለማዘመን በካሜራ የተደገፈ ምርጥ ተሞክሮ ማስፋት ተችሏል። በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴን ጨምሮ ሌሎች የክፍለ ከተማ አመራሮች፣ የአስሩም ወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የክፍለ ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ፅ/ቤት ቡድን አስተባባሪዎች ተገኝተዋል። በዕለቱ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት የሲሲቲ ካሜራ መገጠሙ ዘመናዊ አደረጃጀቱ አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ፣ ግልፀኝነትና ቀልጣፋ አሰራርን ለመዘርጋት እንዲሁም ድጋፍና ክትትልን በማቀላጠፍ ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ሲሉ ተናግረዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለውም በከፍተኛ ቁጭት ሪፎርሙን ለመተግበር ፤አገልግሎቱን ለማዘመን፣ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠር ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ፤አመራሮችና ባለሙያዎች በተጨማሪም ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ የተቀናጀ ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል። የተቀመረውን ምርጥ ተሞክሮ የተዘጋጀውን ሰነድ ያቀረቡት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አማኑኤል ቢሆነኝ ሲሆኑ የተገልጋዩን ህብረተሰብ ጊዜና ጉልበት በመቆጠብ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ስር ነቀል በሆነ መንገድ ለመፍታት ያግዛል ሲሉ ገልጸዋል። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰሮቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ዲሪባ ታደሰ ገለፃውን መነሻ አድርገው በሰጡት ሀሳብ መሰረት አገልግሎቶችን ፍፁም ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድረግ እንደዚህ አይነት ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀምና በማስፋት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ይጠቅማል በማለት የገለፁ ሲሆን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አብርሀም ጠና እንደዚህ አይነት ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በወረዳችን በመጠቀማችንና ለሌሎች ተሞክሮ በማስፋታችን የአገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋና የተገልጋዩን የእርካታ መጠን የተሻለ ለማድረግ ሁነኛ የሆነ ሚና እንደሚጫወት ገልፀዋል። በመጨረሻም የተቀመረውን ተሞክሮ የማስፋፋት ፊርማ ስነ-ስርዓት በማከናወን የዕለቱ መርሃ-ግብር ተጠናቋል።

Search
Recent News