Loading...

ዝርዝር ዜና

ማህበራዊ ማህበራዊ

ትምህርት ቤቶችን ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍሪያ ማዕከላት ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።


ትምህርት ቤቶችን ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍሪያ ማዕከላት  ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።

በስፖርታዊ ውድድሮች መልካም ኢትዮጵያዊ እሴቶችን ማጠናከር ይገባ፤ አቶ ሚሊዮን ኮራ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ከጥር 25 እስከ ሚያዚያ 5/2017በሚደረጉ ስፖርታዊ ውድድሮች የማስፈጸሚያ እቅድ ዙሪያ ከመምህራን፣ከርዕሳነ መምህራንና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ። በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ሁሉም 1ኛና 2ተኛ ደረጃ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የስፖርት ሊግ ውድድር በተማሪዎች በ8 የተለያዩ የስፖርት አይነቶችና በመምህራን በ5 የስፖርት አይነቶች ውድድሩ እንደሚካሄድ በማስፈጸሚያ እቅዱ ላይ ተወያይቷል። በውይይቱ ትምህርት ቤቶች የስፖርት ንቅናቄ መድረኮች የመምራትና የማስተዳደር ልምድ እንዲኖራቸው በማስቻል ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍሪያ ማዕከላት መፍጠርና ስፖርትን በትምህርት ቤቶች ባህል በማድረግ ከሚመለከተው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የጋራ ተደርጓል። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራ እንደተናገሩት በከተማ ደረጃ በሚካሄደው ስፖርታዊ ውድድሮች ጉለሌን በሚመጥን ከፍታ ለመዘጋጀት ሁሉንም ትምህርት ቤቶች መሰረት በማድረግ በፍትሀዊ መልኩ ተማሪዎችና መምህራንን ማወዳደር ያስፈልጋል ካሉ በኋላ ስፖርት በፍላጎትና በተነሳሽነት በማሳተፍ ከትምህርቱ ጎን ለጎን ክበባትን በመደገፍ የሀገራችን ስም ሊያስጠሩ የሚችሉትን ተወዳዳሪዎች ማፍራት ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል። በተጨማሪም በውድድሩ የተሳካ ውጤት ለማምጣት የጸጥታ ሁኔታዎችን፣ስፖርታዊ ስልቶችን፣በስነ ምግባር ዙሪያ የሚታዩትን ኢትዮጵያዊ መረዳዳትና መከባበር ፣መልካም እሴቶችን በስፖርቱ ቤተሰብ በማጠናከር ስፖርታዊ ጨዋነት በመፍጠር ውድድሩን ማከናወን እንደሚገባ ገልጸዋል። በመጨረሻም በክላስተር ደረጃ ከጥር 25 እስከ የካቴት 10፣በክፍለ ከተማ ደረጃ ከየካቴት 14 እስከ 30ና በከተማ ደረጃ ከመጋቢት 5 እስከ ሚያዚያ 5 የሚካሄድ ሲሆን ስፖርታዊ ስነ ምግባርን በመላበስና በፍትሀዊና በፍላጎት በመወዳደር እንዳለባቸውና ለዚህ ደግሞ ሁሉም በቅንጅት መስራት እንዳለበት የጋራ መግባባት ፈጥረዋል።

Search
Recent News