Loading...
Image

አቶ ወልዴ ወገሴ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር

የክፍለ ከተማው ኃላፊ መልዕክት

እንኳን ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዌብሳይት በሰላም መጣችሁ እያልኩ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አሰተዳደር ነዋሪውን የልማትና መልካም አስተዳደር፤ የአገልግሎት አሰጣጥ የተሳለጥ፤ ተደራሽነቱን ለማስፋት እና ለማዘመን በርካታ ስራዎች እየሰራን እንገኛለን፡፡ የመንግስት እና የፓርቲያችን መርህን መሰረት በማድርግ ሰው ተኮር የልማት ተግባራት የዜጎች ፍታሀዊ ተጠቅሚነት ለማረጋገጥ በኑሮ ውድነትና ገበያን በማረጋጋት ፤በሌማት ትሩፋት፣ በስራ እድል ፈጠራ፣ በማዕድ ማጋራት፣ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታና በሌሎች ሰው ተኮር ተግባራት ተጠቃሚነት ላይ እየሰራን እንገኛለን ። አንዲሁም ለማህበረሰቡ ለኑሮ ምቹ እና ውብ የሆነች ክፍለ ከተማ ለመፍጠር የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች በማልማት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ በከተማችን ከተያዙ ፕሮጀክቶች በቁጥርም በስፋትም በቁጥር አንድ ከሚቀመጡ ክ/ከተሞች አንዱ በመሆን ስፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም በርካታ ዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚና የሙያ ባለቤት የሚያደርግ ስራ በመሰራት ላይ ሲሆን በተጨማሪ በክፍለ ከተማችን የአዲስ አበባ መተንፈሻ ሳንባ እደመሆኑዋ መጠን ፅዱና ውብ የማድረግ በተለያየ ጊዜ ማህበረሰቡን በማሳተፍ በንቅናቄ በአካባቢ ፅዳት ማህበረሰባችን እየሰራ ያለውም ጉዳይ ቀላል የማይባልና በአመለካከት እና በተግባር እየመጡ ያሉ ለውጦችም ቀላል የማይባሉ ለውጦች መተዋል እነዚ እና ሌሎች ሁለንተናዊ የሆነ የልማት ስራችን ላይ ያለውን የነቃ ተሳትፎ ለማህበረሰባችን ትልቅ ክብር እዳለኝ መግለፅ እወዳለሁ ፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን የአገልግሎት አሰጣጥ ስራችን ቀልጣፋና ተደረሽ ለማድረግና ስራና ሰራተኛን ለማገናኘት በዋና ዋና ሴክተሮቻችን የሪፎርም ስራ በመስራት የምደባ ስራ የተሰራ ሲሆን የሰው ኃይል በአቅም በክህሎት በቂ ከማድረግና የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ከማዘመን አንፃር የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት በመዘርጋት የተቀናጀ የመረጃ ልውውጥ ስርዓትን እንዲኖር በማድረግ ተገልጋዮችን ከእንግልት በማላቀቅ በቴክኖሎጂ አገልግሎት አማራጭን ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡ እነዚህንና እነዚህን መሰል በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ በትኩረትና በጥራት አዲሁም በመፍጠርና በመፍጠን ስራዎቻችን እየሰራን ሲሆን ሌሎች ክፍለ ከተማችን በሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች የህብረተሰቡን ጥቅም ለማረጋገጥ በምናደርገው ጥረት ሁሉም የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ እያሳሰብኩ በክፍለ ከተማችን ብሎም በከተማችን እድገት በአብሮነትና በጋራ እንድንሰራ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡

180,605

ወንዶች

196,427

ሴቶች

377,032

ጠቅላላ ነዋሪዎች

ኃላፊዎች

የክፍለ ከተማው አመራሮች

Image

አቶ ወልዴ ወገሴ

የጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ

Image

ይከበር ስማቸው አብጤ

የጉለሌ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የጽ/ቤት ኃላፊ

Image

አቶ ሰለሞን ታደሰ

የጉ/ክ/ከ/አስ/ምክ/ዋ/ስ/አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ

Image

ገነት ወጋሪ

የጉ/ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ምክትል እና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ

በክፍለ ከተማው ውስጥ የተከናወኑ ክንውኖች

ዜናዎች

የጉለሌ ክፍለ ከተማ

አስተዳደር

በ2017 ዓ.ም የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰላማዊ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችና ፍላጎቶች በሁሉም ነዋሪዎች በእኩልነት የምታስተናግድ ክፍለ ከተማ ሆኖ ማየት፡፡

በክፍለ ከተማ አስተዳደር ካሉ ክፍለ ከተሞች ተወዳዳሪ በመሆን መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ ለነዋሪዎችዋ ምቹና ተስማሚ የሆነች ክፍለ ከተማ መፍጠር፡፡

- ተጠያቂነት
- ግልጽነት
- ለለውጥ ዝግጁ መሆን
- በዕውነትና በዕውቀት መምራት
- ለላቀ አገልግሎት መትጋት
Image

Get Our App

image description image description